እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

4ኛ ሰንበት ዘአስተምህሮ 2005 ዓ.ም. ሰንበት ዘመጻጕዕ

4ኛ ሰንበት ዘአስተምህሮ 2005 ዓ.ም. ሰንበት ዘመጻጕዕ

መዝሙር፡ ይቤሉ እስራኤል ኢርኢነ ወኢሰማዕነ. . . .
ንባባት፡ 1ቆሮ. 2፡1~ፍ፥ 1ዮሓ፡ 5፡1~6፥ ግ.ሓ.5፡34~ፍ፥ ዮሓ. 9፡1~ፍ። 
ስብከት፡ ደቂቀ እጓለ እመሕያው እስከ ማእዜኑ ታከብዱ ልበክሙ ለምንት ታፈቅሩ ከንቶ ወተሐሱ ሐሰተ፥ አእምሩ ከመ ተሰብሓ እግዚአብሔር በጽድቁ።” መዝ.4፡2። 

Abba Dawitየዛሬው ወንጌል ስለ አንድ ዕውር ሆኖ ስለተወለደ እና ክርስቶስ ዓይኖቹን ጭቃ ቀብቶ ስለፈወሰው ሰው ይናገራል፡፡ (ዮሐ. 9፡1-41)

ይህ ተዓምር በዘመኑና በቦታው በነበሩት ሰዎች ውስጥ የተለየ ስሜትን ፈጥሯል፡፡ በተራው ሕዝብ ውስጥ የመደናገርን ስሜት አሳድሯል፤ ከሚለምንበት ሥፈራ ተነስቶ፣ ያለ መሪ ሲመላለስ በማየታቸው ግራ ተጋቡ፣ ተደናገጡ፤ ምክንያቱም በሕይወት ዘመናቸው እንዲህ ያለ ድንቅ ነገር አይተው አያውቁምና፡፡ ስለዚህ ምስክርነት ከመስጠት እና እግዚአብሔርን ከማክበር ይልቅ ሰውየውን ወደ ፈሪሳውያን መውሰድ መረጡ፡፡

 ፈሪሳውያንም በበኩላቸው የዚህ ምስኪን ሰው ፈውስ ማግኘት ግድ ሳይላቸው በአንጻሩ ጭራሸ በተለያየ ጥያቄ እያደናገሩ የፈወሰውን ኢየሱስን እንዲክድ፣ ልክ እንደነሱ አዳኙን የእግዚአብሔርን አንድያ ልጅ “ኃጢአተኛ” እንዲል ይገፋፉት ጀመር፡፡ ይህ ስላልሆነላቸውም ከምኵራባቸው አባረሩት፡፡

 የዳነው ሰው ወላጆችም ቢሆኑ ከፍርሀት የተነሳ ምስክርነት መስጠት ስላልፈለጉ ኃላፊነቱን ልጃቸው እንዲወጣው ብለው “እርሱ ሙሉ ሰው ነውና ስለሆነው ነገር ራሱ ይመልስ ዘንድ እሱኑ ጠይቁት” በማለት ወደ ኋላ አፈገፈጉ፡፡ ድንቅ የተደረገለት ዓይነ ስውር ግን ያለ ምንም ፍርሃት ጌታውን እና የብርሃን አምላክ የሆነውን ኢየሱስን ማክበር ስለሱም መመስከርን መረጠ፡፡


ከዛሬው ወንጌል ምን እንማራለን?
ማንም ሰው “ለምን እንዲህ ሆኜ ተፈጠርኩ፣ ለምን ይህ ዓይነት ጠባይ ኖረኝ ወዘተ” ብሎ ረብ የሌው ጥያቄ ከማንሳት ይልቅ ማስተካከል እና ማሳመር፣ የሰውን ሕይወት እነዲሻሻል እና እንዲለወጥ ወደሚፈቅደውና በባሕሪው አምላክ ወደሆነው ፈጣሪ መጠጋት ነው፡፡
እምነታችን ብዙ ጊዜ ይፈተን ይሆናል፤ የስራ፣ የትምመህርት፣ የሕይወት አለመሳካት ብዙ ጊዜ የእምነታችንን አቅም ጥያቄ ውስጥ ገብቶ ይሆናል፡፡ ዓመቱ የእምነት ዓመት ተብሎ ተወስኗልና በዚህ በጸጋ ዓመት እንጠቀምበት፡፡ ዓይነ ስውሩ ማየት ተመኘ ይህ መሻቱም እውን ሆነለት፡፡ እኛስ ምን እንዲደረግልን ነው የምንፈልገው? የልባችንን መሻት ስንለምን ግን ባልተከፋፈለ ወይም በጎዶሎ እምነት መሆን የለበትም፣ ጠንካራ እምነት ነው ወደ ፈውስ እና ወደ ስኬታማነት የሚያመጣን፡፡ አንድ ጸጋ ስንጠይቅ ሌላ መማር የሚገባን ነገር ቢኖር ትዕግስት ነው፤ “መጠበቅ” የሚባለውን ነገር መማር እና መለማመድ ይኖርብናል፣ “በለስን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል” እንዲል መጽሐፍ (መጽ. ምሳሌ 27፡18)፡፡ ሁሉ ነገር የሚሆነው እግዚአብሔር ሲወድ እና ሲፈቅድ ብቻ ነው፡፡
የእግዚብሔር ጥበቃ እና የእመቤታችን ቅድሰት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችሁ ጋር ይሁን!

አባ ዳዊት ወርቁ 
ዘማኅበረ ካፑቺን

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት