የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ስም - መስከረም 2
- Category: የእለቱ ቅዱስ
- Published: Monday, 13 September 2021 18:13
- Written by Super User
- Hits: 459
- 13 Sep
የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ስም - Most Holy Name of the Blessed Virgin Mary
መስከረም 2 - የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ስም በአል በአንድ ስፔን ግዛት በ1513 ከዚያም 1671 ወደቀሩት የስፔን ግዛቶችና ኔፕለስ ተዛመተ ። በ1683 ዮሐንስ ሶሚዮሰኪ የተባለው የፖላንድ ንጉሥ ሠራዊቱን ቪዬና በሚባል ቦታ/ከተማ ዳርቻ እያኮበኮበ ከሚመጣው የቁስጥንጢኖስ መሐመድ አራተኛው ሠራዊት ለመመከት አሰማራ። በዚህ ጊዜ ንጉሥ ዮሐንስ ራሱን ለማርያም አደራ በመስጠት እሱና ሰራዊቱ የመጣውን የመሐመድ ጦር በማያዳግም ሁኔታ በድል ተወጡ። ር.ሊ.ጳ. ኢኖሰንት 11ኛ ይህን በአል በመላው ቤተ ክርስቲያን እንዲከበር አደረጉ ።
ትርጉም፦ ዮሴፍ ወልደዮሐንስ