Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መስከረም 3

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - Saint John Chrysostom 

      SaintJohnChrysostom 2     ቅ. ዮሐንስ አፈወርቅ ታላቁ የአንጾኪያ ሰባኪ ከአሥርታት የክህነት አገልግሎት ዓመታት በኋላ ወደ ቁስጥንጢንያ እንዲያገለግል ተወሰደ ። እዚያም እንደደረሰ ያለፍላጎቱ የግዛቱ ጳጳስ እንዲሆን ተደርጎ ተሾመ ። መናኝ፣ የማይጫን ግን የተከበረና በረሐ መነኩሴ እያለ የያዘው የጨጓራ ህመም ላይ እያለ ነው በንጉሣዊ ፖለቲካ ደመና ሥር ሆኖ የተሾመው ።

           ሰውነቱ ደካማ አንደበቱ ግን ኃይለኛ ነበር። ከመጽሐፍ ቅዱስ የወጡ የስብከቱ ይዘቶች ሁልጊዜ ነጥባቸውን ያልሳቱ ነበር። እነዚህ ነጥቦች አንዳንዴ ኃያላንና ከፍተኝ ቦታ ላይ ያሉትን የሚነድፍ ነበር። አንዳንድ ስብከቶቹ እስከ ሁለት ሰዓታት ይቆዩ ነበር።

           የአኗኗሩ ሁኔታም በብዙ የንጉሡ ባለሟሎች አይሞገስም ነበር። ቅ. ዮሐንስ ከከፍተኛ የመንግሥት አባላት የበለጠ ቅድሚያ ስለተሰጠው የተሰማውን ቅሬታ አሳውቋል ። በአንድ ቦታ ተወስኖ የማይቀመጥም ሰው አይደለም ።

           ቅንዓትም ስላለው ወሳኝ የሆኑትን እርምጃዎች ወስዷል። ጵጵስናን በጉቦ ያገኙትን ሁሉ አስወግዷል። አብዛኛው ስብከቶቹም ሐብታሞች ያላቸውን ሐብት እንዴት ከድሆች ጋር መካፈል እንዳለባቸው በነጥብ አስቀምጧል። ቅ. ዮሐንስ የግል ሀብት የመጣው በአዳም ኃጢአትም ምክንያት ነው በማለቱና ሐብታሞችም ይህን በመስማታቸው ቅራኔያቸውን አሰምተዋል ። እንዲሁም ያገቡ ወንዶች የጋብቻቸውን ታማኝነት ልክ እንደ ባለቤታቸው መጠበቅ እንዳላቸው አሳስቧል። ፍትሕና በጎ አድርጊነትን በሚመለከት የማያወላውል ውሳኔዎችን አድርጓል።

           ቅ.ዮሐንስ በሚሰብክበት ጊዜ ኩሩ፣ ታታሪ፣ ግልፅ ተናጋሪም ነበር ። በርግጥም ነቀፋና በግል ችግሮች ኢላማ ውስጥ ገብቶ ነበር። ያለመጠን ወይን ይጠጣል እንዲሁም ጥራት ያለው ምግብ ይመገባል እያሉ ይከሱትም ነበር። የአንድ ሀብታም ጋለሞታም ኦሊምፒያ የምትባል የመንፈሳዊ አባት/መሪም በመሆኑ ትንኮሳና ሐሜቶች ይወረወሩበት ነበር፤ እንዲሁም ግብዝናውን፣ ሐብትንና፣ ንጽሕናን/ድንግልውን በሚመለከት ብዙ ያወሩበት ነበር። ትንሿ እስያ (ቱርክ) ላይ በሚገኙ ጳጳስትም ላይ የወሰደውን እርምጃ እንደስግብግብነትና ከቀኖናዊ ስልጣኑ ውጭ ነው ብለው አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን ባለስልጣናት ተመልክተውታል።

           ቴዎፍሎስ የአሌክሳንድሪያ ሊቀ ጳጳስና ንግሥት ዮዲክሲያ ቅ. ዮሐንስን ለመጣል ወሰኑ። ቴዎፍሎስ የቁስጥንጢንያ ጳጳስ ያለው አስፈላጊነት እያደገ ሲመጣ፣ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ቅ. ዮሐንስን መናፈቅነትን ያስፋፋል ብሎ ከሰሰው። ቴዎፍሎስና ሌሎች የተናደዱ ጳጳሳት በንግሥቲቱ ዮዲክሲያ ይታገዙ ነበር። ቅ.ዮሐንስ በወንጌል ስብከቱ ስለዋጋ ትምህርት ሲሰጥ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ካለው ሀብት ጋር በማወዳደሩ ንግሥቲቱ ትጠላው ነበር። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ስብከቱ አስፈሪው ጄዜቤልና እምነት የለሹ ሄሮድያስ ከንግሥቲቱ ጋር ያዛምዳት ነበር። ይህ በመሆኑ ቅ. ዮሐንስን ለስደት ለመዳረግ በቃች። በስደት ላይ እንዳለም በ407 ዓ.ም. አረፈ ።

ትርጉም፦ ዮሴፍ ወልደዮሐንስ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።