Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የዘጠኝ ቀን ዝግጅት (ቅዱስ ዮሴፍ) ቀን 3

St Joseph Novena 2013 33ኛ ቀን - ቅዱስ ዮሴፍ ፡ በቅድስት ሥላሴ የተመረጠ ሰው (ጸሎተ ተሰዓቱ - ኖቬና)

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ አንተ በእግዚአብሔር አብ የተመረጥክ ሰው ነበርክ፡፡ በምድርም ላይ የእርሱ ተወካይ እንደትሆን መረጠህ፡፡ ስለዚህም የእርሱ ብቁ ተወካይ እንድትሆን የሚያስፈልጉህን ፀጋና በረከት ሰጠህ፡፡ አንተ በወልደ እግዚአብሔር የተመረጥክ ሰው ነበርክ፡፡ በዚሁም ምክንያት የራሱን ሀብታና ጸጋ በተለየም ፍቅሩን ጨመረልህ፡፡ እውነተኛ ቅድስናህን የሚለካው የኢየሱስ ህያው ምስል በመሆንህ ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ አንተ በአጠገቡ ሆንህ በመሥራት በጎ ተግባርህን እለታዊ ሥራን፣ ሥቃይና ሕይወትህን ጭምር ለእርሱ በማቅረብ ሙሉ በሙሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰጥተሃል፡፡ አንተ ፍጹም በሆነ መልክ ኢየሱስን ትመስል ዘንድ እርሱ ፍጹም በሆነ መልኩ በአንተ ውስጥ ኖረ፡፡ ይህም ልዩ የሆነ ክብርህና ቅድስናህ መሠረት ነው፡፡ ስለዚህም ከቅድስት ድንግል ማረያም ቀጥሎ ቅድስናህ ከሌሎች ቅዱሳን ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ አንተ በመንፈስ ቅዱስ የተመረጥክ ሰው ነህ፡፡ እርሱም የቅድስት ሥላሴ ልብ በመሆን የአብ እና የወልድ የርስ በርስ ፍቅር ነው። በጥበቡም ፍጥረቶችን ሁሉ። ከኢምንት ፈጠሮ አቅጣጫም እያስያአዛቸው ወደ ግብ ለመድረስ የሚያስፈልጋቸውንም ጸጋ እየሰጣቸው ወደ ተፈጠሩበት ዓላማ ይመራቸዋል። ማንኛውም ጥሪና የጥሪውን ግዴታ በብቃት መወጣት የሚመነጨው ከመንፈስ ቅዱስ ነው። እንደ ኢየሱስ ሕጋዊ አባትና የቅድስት ቤተስብ ራስ በጣም ከፍ ያለና የላቀ ኃላፊነትን የሚጠይቅ ጥሪ ነበረህ፤ ማለትም ወልደ እግዚአብሔርን በመንከባከብና በማሳደግ ለዓለም የደኅንነት መንገድ በመክፈት፡፡ በዚህ ሥራህ የመንፈስ ቅዱስ መሣሪያ ሆንህ አገለገልክ፡፡ ቅዱስ መንፈሱ እየመራህ በታላቅ ታዛዥነትና ፍቅር ሥራውን አከናወንክ፡፡

ፈርዖን እስራኤልን ከግብጽ ስላወጣው የቀድሞ ዮሴፍ የተናገረው ስለአንተ ይተነገረ ትንቢት ነው፡፡ “በእውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን እንደዚህ ያለ ሰው እናገኛለንን?” /ዘፍ 41፡38/ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ በመለኮታዊ ሥራ የነበረህ ድርሻ ከቀደሞ ዮሴፍ ድርሻ አያንስም፡፡ ዛሬም አንተ ከልጅህ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በሰማይ ሆንህ ክብሩን ታያልህ፤ ስለኛም ትጸልያለህ፡፡

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ በራሱ በልዩ ሁኔታ የተመረጠ ሰው ስላደረግህ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ የአንተን ቅድስና ፈለግ እንድንከተልና እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንድችል ፀጋ አሰጠን፡፡ ራሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ እቅድ በማስገዛት ወደ መንግሥተ ሰማይ እንደንበቃና ዘለዓለማዊ ሕይወትን እንደንቀዳጅ እርዳን፡፡አሜን፡፡

እጅግ ጻድቅ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ - ለምንልን፡፡

(በየዕለቱ የሚደገም)

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ እኔ ደካማው ልጅህ ሰላም እልሃለሁ፡፡ አንተ የሚወዱህንና የሚያክብሩህን ትከላከላለህ፤ ታማልዳቸዋልህ፡፡ በአንተ ላይ ልዩ የሆነ መታመን እንዳለኝና ከአዳኜ ኢየሱስና ከቅድስት እናቱ በመቀጠል የደኅንነት ተስፋዬ አንተ ነህ፡፡ ምክንያቱም አንተ የእግዚአብሔር ወዳጆችን ለመርዳት ከቶ አታመነታም፡፡ ስለዚህም በትህትና ስምህን እጥራለሁ፡፡ ከምወዳቸው እና የቅድስት ቤተስብ አፍቃሪ ከሆኑት ጋር አማላጅነትህን በመተማመን ወደ አንተ እንቀርባለን፡፡ ለአዳኛችን ኢየሱስና ለወላዲተ አምላክ ባለህ ፍቅር በዚህች አለም እስካለንና በሞታችን ጊዜ እንዳትለየን እንለምንሃለን፡፡

የእመቤታችን ቅድስት ደንግል ማርያም እጮኛ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ንጹሕ፣ ትሑት፣ በቸርነት የተሞላ አዕምሮና ፍጹም ለእግዚአብሔር ፈቃድ የመገዛት ጸጋ አሰጠኝ፡፡ አንተ በኢየሱስና በድንግል ማርያም እጅ እንደትክ እኔም ተመሳሳይ ዕድል ያጋጥመኝ ዘንድ መሪ፣ አርአያ እና አባት ሁንኝ፡፡

አፍቃሪና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ተከታይ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ለመንፈሳዊና ለየእለቱ በጎነት በተለይ ደግሞ መልካም ሞት አገኝ ዘንድ በዚህች ሰዓት በልቤ ውስጥ ያለውን አሳብ አስፈላጊ የሆኑትን ጸጋዎች ከኢየሱስ መለኮታዊ ልብ ታሰጠኝ ዘንድ አማላጅነትህን እማጸንህለሁ፡፡

/እዚህ ላይ በልብ ያለውን አሳብ መጥቀስ/

ሥጋ የለብሰው ቃል ጠባቂ ስለእኔ የምታቀርበው ጸሎት በእግዚአበሔር ፊት እንደሚሰማ እተማመናለሁ፡ አሜን፡፡

የቅድስት ድንግል ማርያም እጮኛ፣ አፍቃሪና ጠባቂ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ጥበቃህናን እርዳታህን የፈለገ፣ መጽናናትን ሳያገኘ የቀረ ማንም የለም፡፡ በቅዱስነትህ በመተማመን እነሆ ወደ ፊትህ እቀርባለሁ፡፡ የመድኃኒታችን ምድራዊ አባት ሆይ ልመናዬን በቸርነት ተቀበለኝ እንጂ ችላ አትበለኝ፡፡ አሜን፡፡

የቅዱስ ዮሴፍ መዝሙር

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ጠብቀን

ወደ ገነትም አድርሰን፡፡

.

እጅግ ክቡር ዮሴፍ

ሲፈረድ በምድር ላይ

ለነፍሳችን እዘን

ተስፋ አድርገናል አንተን፡፡

 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት