እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel
እንኳን ደህና መጡ!
በዚህ ድረ ገጽ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሕይወት፣ እምነትና ትምህርትን በእውነትና በመንፈስ እየተማሩ፣ እየኖሩና እየመሰከሩ ከእኛ ጋር ይጓዙ!
“የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙርነት ደስታ እንደገና...

By Super User

22 January, 2024

“የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙርነት ደስታ እንደገና...

“የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙርነት ደስታ እንደገና ሊሰማን ይገባል!” ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሑድ ጥር 5/2016 ዓ. ም. በቅዱስ...

ሲቶ የመጽሐፍትና ንዋያተ ቅዱሳት መደብር ተመረቀ

By Super User

09 January, 2024

ሲቶ የመጽሐፍትና ንዋያተ ቅዱሳት መደብር ተመረቀ

የሲታውያን ወንድሞች ገዳም የሆነው “ሲቶ የመጽሐፍትና ንዋየ ቅዱሳት መደብር” ዛሬ ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም. ተመረቀ። በአዲስ አበባ...

የምንኩስና መሐላ በቅ. ዮሴፍ ዘሲታውያን

By Super User

09 January, 2024

የምንኩስና መሐላ በቅ. ዮሴፍ ዘሲታውያን

እሑድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ወንድም ፍቃደ ሥላሴ (ፍቃዱ) ተስፋዬ እና ወንድም ሉቃስ (ብርሃኑ) ቡናሮ በአዲስ አበባ ቅ. ዮሴፍ ገዳም...

ዘአስተምሕሮ 2ኛ

ዘላለማዊነትን በዘመናዊነት መለወጥ!

ዮሐ.5:16-27 ቆላ.1:12-29 1ጴጥ.1:13-20 ሐዋ.19:21-40

Ab Weldየዛሬው ወንጌል ክርስቶስ ከአይሁዳውያን ጋር ያደረገውን ንግግር በመተረክ ስለ እግዚአብሔር ቀጣይ ምሕረት እንድናስተነትን ይጋብዘናል። ኢየሱስ ሠላሳ ስምንት ዓመት ሙሉ የታመመን አንድ ሰው በዓይናቸው ፊት ከፈወሰ በኋላ አይሁዳውያን ኢየሱስን ያሳድዱት ጀመር። ኢየሱስ ግን "አባቴ ሁልጊዜ ይሠራል፤ እኔም እሠራለሁ" ሲል መለሰላቸው (5:17)። ይህንን የኢየሱስ መልስ በሰሙ ጊዜ አይሁዳውያን ኢየሱስን ይገድሉ ዘንድ ይበልጥ ተነሣሡ። ምክንያቱም ይላል ወንጌል ሰንበትን በመሻሩ ብቻ ሳይሆን "እግዚአብሔር አባቴ ነው" በማለቱ ነበር።

ሰው ለምን በእግዚአብሔር መልካም ሥራ አይደሰትም ብለን ብንጠይቅ ብዙ ምላሽ ይኖር ይሆናል፤ ግን ሰው የራሱ ሥራ ክፉ በሆነና እግዚአብሔርን እንደሚያሳዝን ባወቀ መጠን ሆኖም ግን ወደ ቀና መንገድ መዞር መምረጥን ካልፈለገ እግዚአብሔር ለሌሎች ሰዎች በሚያደርግላቸው መልካም ነገር ሁሉ ያዝናል። የሌሎቹ መልካምነት የርሱን ጎዶሎነት ያስታውሰዋልና መልካም ነገሮችን በይፋ መቃወም ይጀምራል። አባት፣ አባባ ብለን እንጠራው ዘንድ የተሰጠንን ጸጋ በመርሳት እግዚአብሔርን አባት ያለማድረግ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም አባት መሆኑን እንቃወማለን። አይሁዳውያን ከነበራቸው የሃይማኖታቸው ግንዛቤ ባሻገር የመመጻደቅ ድርጊቶቻቸው የእግዚአብሔርን ሥራ እንዳያዩ ጋርዷቸው ነበር።

የኛን ውስጣዊ የእግዚአብሔር ስዕል በመጠኑ እንይ። ክርስቶስ "አባታችን ሆይ!" ብላችሁ ጸልዩ ብሎ ሲያዘንና "የሰማይ አባታችሁ" ብሎ ሲያስተምረን "እግዚአብሔር አባቴ ነው" የሚለውን እወጃ ለኛም ሰጥቶናል። ክርስቶስ ከአባቱ ጋር ያለው ብቸኛ የልጅነት ደረጃን ባይሆንም የጸጋ ልጅነት ተሰጥቶናል፤ ታዲያ አፋችንን ሞልተን "እግዚአብሔር አባቴ ነው" ማለት እንችል ይሆን?

ይህን ማለት መቻል በሌላ አባባል እኔ የእግዚአብሔር ነኝ የሚል መልእክት ማስተላለፍ ማለት ነው። ዛሬ ዛሬ እኔ የእግዚአብሔር ነኝ ማለት በማኅበረሰባችን ውስጥ ብዙ ቅጽል ነገሮችን የሚያሰጥ ስለሆነ የዘመናዊነት ክፍል መሆን እፈልጋለሁ ብሎ የሚያስብ ሰው የእግዚአብሔርን አባትነት በይፋ ሕይወቱ ማወጅ ብዙም አይዋጥለትም። ይህ አካሄድ ግን ድምዳሜው ላይ ሲደርስ መዘዙ ዘላለማዊንትን በዘመናዊነት መቀየር ይሆናል። ይህ በሕይወቴ ይታያል ወይ በማለት እናስተንትን።

እግዚአብሔር አባቴ ነው ማለት ትልቅ ምስጢር ውስጥ ራስን ማስገባት ማለት ነው። ክርስቶስ ወንድሜ፣ ቅድስት ድንግል ማርያም እናቴ፣ መላእክቶች ጠባቂዬ፣ ቅዱሳኖች አማላጆቼ ማለት ነው። የእሱን አባትነት ተቀብሎ ሌሎቹን ማስወገድ ያስቸግራል፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቤተሰብ ስፋት እኛ ከምንገምተው በላይ እርስ በርስ የተሳሰሩና ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለው እጅና እግር አንዱ ለአንዱ እንደሚረዳ እንዲሁ የተጠማመረ ኅብረት ያለው ነው። እስቲ ይህን ምስጢር እናስበው፤ ደካማነታችን ዓይናችንን ጋርዶን ራሳችንን ብቻ በሚያሳየን ሰዓት የእንደዚህ ዓይነት ትልቅ ቤተሰብ አባል መሆናችን ትልቅ ጸጋ መሆኑን እናስታውስ። ተፈጥረን በዚች ፕላኔት ተውጠን እንድንቀር አይደለም የእግዚአብሔር ፈቃድ። የዚች ዓለም ውስንነት መልእክት ሁልጊዜ ከዚህም በላይ ሕይወት አለ የሚል ነው። የእርሱ ልጅ መሆናችን ገድበው ከያዙን ነገሮች ላቅ ያለ ዓላማና ውሳኔ እንዲኖረን ይጋብዘናል።

ጠንካራ የሚመስለው ሰው ሲወድቅ፣ ሀብታሙ ሀብቱን ትቶ ከምድር ሲሰናበት፤ ነገሮች ሁሉ ቁርጥራጭ ሆነው ሲታዩን ማንነታችንን ወደ ሕያው ከፍታ የሚያነሳው ብቸኛ እውነት የእግዚአብሔር ልጅ መሆናቸን ነው። ይህ ባይሆን በርግጥ ምድር ከመልስ ይልቅ ጥያቄን የምታበዛ መቆያ ቦታ ብቻ ሆና ተስፋ ባሳጣችን ነበር። ነገር ግን ይህች ዓለም እናተርፍባት ዘንድ ተሰጥታናለች፤ ከርሷ የበለጠውን እናገኝ ዘንድ ወደርሷ መጥተናል እንጂ እርሷን አግኝንተን ከርስዋ የበለጠውን እንድናጣ አይደለም። ክርስቶስ "ሰው ዓለሙ ሁሉ የእርሱ ቢሆንና ነፍሱን ግን ቢያጠፋ ምን ይጠቅመዋል" (ማቴ.16:26) እንዳለው ነው። "እግዚአብሔር አባቴ ነው" ማለት የዚችን ምድር ነገር ለቀቅ ለቀቅ ማድረግ ማለት ነው። ቅዱስ አውጎስጢኖስ ዕድሜያችን ዘላለማዊነትን እናገኝበት ዘንድ ተሰጥቶናል እንጂ ምድራዊውን ኑሮ ብቻ እንኖር ዘንድ አይደለም፤ ለምድራዊ ኑሮ ብቻ የተፈጠርን ከሆንንማ ይህች ዕድሜያችን በጣም አጭር ናት ይላል።

ውሏችንን ስንጀምር "እግዚአብሔር አባቴ ነው" ብለን እንውጣ፣ ስንውልም ሆነ ውሏችንን ስንደመድም "እግዚአብሔር አባቴ ነው" ብለን እናስብ። ምናልባትም ይህን በምናነብበት ሰዓት ራሱ አቋርጠን "እግዚአብሔር አባቴ ነው" እንበል......። ማን ያውቃል ይህን ማለት የሚከብደን ሁኔታ ውስጥ ልንሆን እንችላለን፤ እግዚአብሔር ግን ከሁኔታዎች በላይ ነውና አባትነቱ አይቀየርም። ስለዚህ ውስጣችን ቢዝል፣ ተስፋ ማድረግ ቢሳነን፣ ከኃጢአታችን ጋር ያለን ቁርኝት የበረታብን ቢመስለን፣ የኑሯችን ደባል ራሱ ብቸኝነት ሆኖ በሚሰማን ሰዓት.....ሁሉ ኢየሱስ ሊያጠምዱት በሚያሳድዱት ፊት የሰጠው መልስ በአንደበታችን ይሁን:- "እግዚአብሔር አባቴ ነው"።

ኢየሱስ ለአይሁዳውያን ሲመልስላቸው "አባቴ ሁልጊዜ ይሠራል" አላቸው። ይሄኮ ለሰው ሁሉ መልካም ብስራት መሆን የሚገባው ነገር ነው። ከመደሰት ይልቅ ሁሌ ይሠራል ስላላቸው ያሳድዱት ጀመር። እግዚአብሔር የማይሠራበት ጊዜ ቢኖር ምን ይውጠን ነበር። ኢየሱስን አይሁዳውያን ሰንበት ነውና ምንም አትሥራ ሲሉት፤ እሱ ግን "ሁልጊዜ" መሥራት እንዳለበት ያውቃልና እንደ አምላክነቱ ለሰው ልጅ በጎን ከማድረግ ምንም እንደማይገታው አስረዳቸው።

አንዳንዴ የሰው ልጅ እግዚአብሔር እንዳይሠራ የሚፈልግበት ጊዜ ሊኖር ይችላል ብለን ካሰብን ክፉን ስናደርግ ወይም ማድረግ ስንፈልግ ብቻ ሊሆን ይችላል፤ ግን እሱ ሁሌም ይሠራል። ክፋትን ስናደርግም ቢሆን እሱ ይሠራል፦ የእሱ ሥራ ምሕረት ነው። በምንፈልገውም በማንፈልገውም ጊዜና ቦታ፣ የዕድሜ ደረጃና የአናኗር ዘይቤያችን ሁሉ እሱ ሁልጊዜ ይሠራል፣ ሁልጊዜ ይቅር ይላል። ቤኔዲክቶስ 16ኛው "እግዚአብሔር ሲገባበት በረሃው ለምለም ይሆናል" እንዳሉት የደረቀና የጠወለገ መንፈሳዊነታችንን እሱ እንዲያለመልምልንና የእርሱ ልጅ የመሆናችንን ክብር ዳግም እንጎናጸፍ ዘንድ ከርሱ ሰፊ ቤተሰብ ጋር የቃሉና የማዕዱ ተካፋይ እንሁን፤ ሁልጊዜ የሚሠራ አባት ሊሆነን ስለፈቀደም የተመሰገነ ይሁን።

ወደ ቤት መመለስ

Churchቶሊከ የሚለው ስም ሁነኛ ትርጉሙ ጠቅላላ፣ ሁላዊነት፣ ሁሉን አቀፍ... የሚል ጽንሰ ሃሳብ የሚያስተላልፍ ሲሆን መሠረቱም ካቶሊኮስ ከሚል የግሪክ ቃል የተወረሰ ነው።

ቤተ ክርስቲያን በጥንታዊው ዓለም በኃያልነት ተንሰራፍቶ በነበረው የሮማ ግዛት ሙሉ ለሙሉ ተሰራጭታ ትገኝ ስለነበረና "እስከ ዓለም ዳርቻዊ" /ሐዋ 1:8/ ከሆነ ባህርይዋ ካቶሊክ የሚል ስያሜን በዚያን ዘመን አገኘች።

በቤተ ክርስቲያን ታሪክም ለመጀመሪያ ጊዜ ካቶሊክ የሚለው ቅጽል ለቤተ ክርስቲያን ተሰጥቶ የምናገኘው በ110 ዓ.ም. ገደማ በቅዱስ ኢግናጽዮስ ዘአንጾኪያው ጽሑፍ ውስጥ ነው።

በዚህች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኘውን በመሥራቿና መሠረቷ ከሆነው ከክርስቶስ የሚመነጨውን ዘመን ጠገብና ዘመን ተሻጋሪ ሀብት ይቋደሱ።ተጨማሪ ያንብቡ

እኛነታችን

ስለ እምነታችን እንወያይ!

show10በእምነታችን ዙሪያ ስለተለያዩ አንቀጸ እምነቶቻችን፣ አስተምህሮዎች፣ በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በሥርዓተ አምልኮ፣ በጸሎት ሕይወት፣ በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ፤ በምሥጢራት፣ ስለ ተለያዩ መንፈሳዊነቶቻችን፣ ስለ ቅዱሳን፤ ስለ ፍልስፍና…እንወያይ።

እንዲሁም የተለያዩ ዓይነት ጥያቄዎች ካሉን ወደዚህ የውይይት መድረክ ተመዝግበን በመግባት እንጠያየቅ፣ እንወያይ፣ እምነታችንን እናጠናክር።ይህንን በመጫን ይግቡ


 ገጾቻችን ውስጥ…
በድረ ገጻችን ውስጥ ሊያገኟቸው ከሚችሉ ብዙ የጽሑፍ፣ የድምፅና የምስል ትምህርቶች፣ ታሪኮች፣ ጥናቶች፣ አስተንትኖዎች... በጥቂቱ
 
ቃልህ ለእግሬ ብርሃን ነው

ቃልህ ለእግሬ ብርሃን ነው

የየሰንበቱ ወንጌል በዚህ ክፍል ውስጥ ይሰበካል

አዘጋጆቹ
አዘጋጆቹ
ካቶሊካዊነት

ካቶሊካዊነት

ክርስትናችንን ከካቶሊካዊነታችን ማንነት የምንቃኝበት ክፍል ሲሆን እምነታችንን ለማወቅ እንተጋበታለን።

አዘጋጆቹ
አዘጋጆቹ
ክርስቲያናዊ ቤተሰብ

ክርስቲያናዊ ቤተሰብ

ቤተሰብ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ያለውን እውነታና ለዚህም የክርስቲያናዊ ጋብቻ ምስጢር፣ ልጆችን የመውለድና የማሳደግ ኃላፊነት…

አዘጋጆቹ
አዘጋጆቹ
የቤተ ክርስቲያን ትምህርት

የቤተ ክርስቲያን ትምህርት

ስለ ሰባቱ ምስጢራትና ልዩ ልዩ የእምነታችን አርእስት ይዳሰሳሉ

ካተኪስት
ካተኪስት
በድምፅና ምስል የተዘጋጁ መጻሕፍት፣ መዝሙሮች፣ ጸሎቶችና ትምህርቶች

በድምፅና ምስል የተዘጋጁ መጻሕፍት፣ መዝሙሮች፣ ጸሎቶችና ትምህርቶች

መንፈሳዊ ሀብቶች በድምፅና በምስል የሚሰበሰቡበት ክፍል ሲሆን በአማርኛ የተጻፉ መንፈሳዊ መጻሕፍትን፣ ጸሎቶችን…ማየትም ሆነ በድምፅ ለመስማት ይችላሉ።

አዘጋጆቹ
አዘጋጆቹ
ጸልይ ሥራም!

ጸልይ ሥራም!

የምንኩስና ሕይወት እንደ ክርስትና የፍጽምና ጉዞ ያለው ትርጉምና ታሪካዊ አመጣጥ…

አባ ዘሲቶ
አባ ዘሲቶ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት - ብሉይና አዲስ ኪዳናት 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት