እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

እግዚአብሔር ቁጡ አይደለም

እግዚአብሔር ቁጡ አይደለም

የእኛ እግዚአብሔር እኛ ከምናስበው እጅግ የተለየ ነው፡፡ እግዚአብሔር ፍትሕ ስለሆነ ለበደልነው ሁሉ ካሳ እንደሚፈልግ ብዙ ጊዜ ሰምተናል፡፡ ነገር ግን የእኛ እግዚአብሔር ፍትሕ ብቻ ሳይሆን ፍቅርም ነው!

እግዚአብሔርን ከእኛ ጋር ማስታረቅ አያስፈልገንም፡፡ ምክንያቱም እርሱ ራሱ እርቅ እና ይቅርታ ነውና፡፡ እኛ ነን ፊታችንን ከእግዚአብሔር የምናዞረው እንጂእግዚአብሔርማ እይታውን ከእኛ ላይ በፍጹም አንስቶ አያውቅም፡፡ እግዚአብሔር ወደ እርሱ እንድንመለስ እየጠበቀን ነው፣ እንዲያውም እኛን ለመገናኘት ወደ እኛ እየሮጠ መሆኑን ልንክዳቸው የማይቻለን ጠንካራ የፍቅር ማስረጃዎቹ ይመሰክራሉ፡፡

እኛ አይደለንም የእግዚአብሔርን ቁጣ የምናስታግሰው፣ እግዚአብሔር አልተቆጣንምና ነው፡፡ ፍቅር አይበሳጭም(1ኛ ቆሮ 13፡5)፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር ነው የሰው ልጅን ቁጣ ለማብረድ የሚጥረው፡፡ ነገር ግን ይህንን ማሳካት አልቻለም ምክንያቱም የሰው ልጅ አሁንም በእግዚአብሔር ላይ እንደተቆጣ ነውና፡፡ በዘመናችን ሰብዓዊ ተፈጥሮ በእግዚአብሔር ላይ እንደአሁኑ ከፍቶ ያውቃልን? ከዚህ በፊት ባልታየ መልኩ እግዚአብሔር እየተወቀሰ ይገኛል፤ይህንን ያህል ክፉ ነገር እንዲከሰት የሚፈቅድ እርሱ ምን ዓይነት እግዚአብሔር ነው?

አብዛኛው በእግዚአብሔር ላይ የሚደረግ የሰው ልጅ አመጽ እውነታው ሲታይ የሚያመለክተው እኛ የምንስለውን እግዚአብሔር ባህርይ ማለትም፡- ክስ የሚመሰርት እግዚአብሔርና ለመቅጣት ጥሩ አጋጣሚ የሚጠባበቅ አምላክን ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ እግዚአብሔር ግን የሚፈራና የሚጠላ ነው፡፡ ያለ ምንም ተቃውሞ በመስቀል ላይ የተሰቀለውና እጆቹ ሁሉንም ለማቀፍ በሰፊው የተዘረጉት አምላክ፣ ሰዎችን ሁሉ ከእርሱ ጋር እንዲሁም እርስ በእርሳቸው አንድ ለማድረግ በብርቱ ይተጋል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ እግዚአብሔር ደግሞ ለማፍቀር አይከብድም /አያስቸግርም!!/

ምንጭ፡ This is the day the Lord has made, 365 daily meditations: By         Wilfrid Stinissen)

አባ ተሻለ ንማኒ - ሲታዊ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት