እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ግንቦት 26 2004 ዓ.ም - ቡሩክ በዓል ጰራቅሊጦስ

ግንቦት 26 2004 ዓ.ም - ቡሩክ በዓል ጰራቅሊጦስ

1ቆሮ 15፡ 2ዐ-34 1ጴጥ 1፡1-12 ዮሐንስ 2ዐ፡1-23

ሁለት ነጫጭ ልብስ የለበሱ መላእክት ጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በተቀበረበት መቃብር እግርጌና እራስጌ ተቀምጠው አንቺ ሴት ስለምን ታለቅሻለሽ ብለው ማርያምን ይቀይቋታል፤ ጌታዬን ወስደውታል ወዴት እንዳኖሩት አላውቅም ብላም ትመልስላቸዋለች ያንጊዜ ነበር ኢየሱስ "ማርያም" ብሎ ጠራት እርሷም ዘወር ብላ ረቡኒ በዕብራይስጥ መምህር ማለት ነው" ነጫጭ ልብስ የለበሱት መላእክት እንደ አለባበሳቸው ደስታን አብሳሪ ብርሃንን ፈንጣቂ ተስፋን የሚገልጥ መልዕክትን የያዙ ናቸው፡፡ በደስታ ተሞልተው ደስታን የሚያበስሩ ዛሬም መላዕክቱ ደስታን የሚያበስሯት መግደላዊት ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰባት አጋንንት ያወጣላትንና ከስቃይ ካዳናት በኋላ የክርስቶስ አገልጋይ የነበቀበሩ ምና የመረች ስትሆን የስቅለስክር የሆነች እንዲሁም ከሞት ከተነሳ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስቶስ የታያት ትልቅ አገልጋይ ነበረች፡፡ የዛሬውም ወንጌል ይህንኑ በሰፊው ያሳየናል፡፡ ማርያም መግደላዊት የተደረገላትን ውለታ ቆጥራ የክርስቶስ አልጋይ ነበረች እስከመስቀሉና ሕማማቱን ተካፍላለች፡፡ ከእነዚህ አገልጋዮች ዛሬ እኛ ልንማር የሚገባን ብዙ ነገሮች አሉን፡፡ ማርያም መግደላዊት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ስር ስር እየተከተለች ስቃዩን ሁሉ ተካፋይ ነበረች፡፡ ዛሬ እኛስ የወንድሞቻችን ችግር፣ ሐዘን፣ ሕመም እንካፈላለን ዋናው ከክርስቶስ ጋር መሆንና የክርስቶስን ሕይወት ተካፋይ ከሆንን የነዚህን የወንድሞቻችንን ነገሮች ሁሉ መሸከም ይገባናል፡፡

ምንባቡ ስለ ምን ይናገራል?

እንደ ማርያም መግደላዊት ተደረገልንን እናውቃለን?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት - ብሉይና አዲስ ኪዳናት 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት