ሚያዚያ 28ቀን /2004 ዓ.ም - እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው
- Category: በአ. አ. ካቶሊካዊ ሰበካ (A.C.S.) የተዘጋጁ የሰናብት አስተንትኖዎች
- Published: Sunday, 06 May 2012 09:30
- Written by Super User
- Hits: 2813
- 06 May
ሚያዚያ 28ቀን /2004 ዓ.ም - እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው
ቆላ 3፡5-17 1ጴጥ 3 ፡15-22 ሉቃ 24፡36-49
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው፡፡ እነዚህ እግሮቹ እና እጆቹ በመስቀለ ላይ ተቸንክረው ነበር፡፡ እርሱም ለዘለዓለም የማይጠፋ ምልክት እና መድኃኒት ነው፡፡ ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳ መሆኑን ያምኑ ዘንድ የትንሳኤው አካል መሆኑን እጁንና እግሩን ካሳያቸው በኋላ በፊታቸው ምግብ በመብላት ማንነቱን ገለጸላቸው፡፡ እነርሱም ፍጹም በሆነ እምነት አመኑ፡፡ የክርስቶስ ትንሳኤ ለእርሱ በማመን ያንቀላፉት ሁሉ በመጨረሻ የሚሱበት ምልክት ነው፤ ከትንሳኤ በኋላ የአዳኛችን ፊት አነጋገር ባሕርይ ሁሉ ከመሞቱ አስቀድሞ ሐዋርያቱ ያውቁት እንደነበረው አልነበረም፡፡ ከሞት በኋላ እንለመጣለን፡፡ ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ እንዲሁ እርሱን የሚያምኑት ሁሉ ይድናሉ ከሞትም ይነሳሉ፡፡ ሰዎች ከሞት በኋላ በሚመጣው ሕይወት የሰው ልጅ መልክ ምን እንደሚመስል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሳይቶናል ሰውነታቸው መንፈሳዊ አካል ተላብሶ እንለወጣለን፡፡ በመቀጠልም ክርስቶስ መከራ ይበቀላል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሳል በስሙም ንስሐ እና የኃጥያት ሥርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል፡፡ ጌታ ራሱ ስለእኛ ሞት ተነስቷል በሕይወታችን የወደቀብንን የመቃብር ድንጋይ ማንከባለል እንችል ዘንድ እርሱ ራሱ ይረዳናል፡፡ በእርሱ ዘንድ በንስሐ ሙሉ ስርየት ኃጢአት ማግኘት እንችል ዘንድ ሞቷል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም "እኔ ለዓለም የሞትኩ ነኝ ዓለምም በእኔ ዘንድ የሞተች ናት" ይላል፡፡ ሐዋርያው ይህንን ቃል የተናገረው የዓለምን ነገር በምንም መልኩ የለሁበትም ማለቱ ሳይሆን ኃጥያትን ላለመስራት ቁርጥ ፍቃድ አድርጌአለሁ ማለቱ ነው፡፡
እኛም በዚህ ዓለም እስካለን ድረስ በኃጥያታችን እየተጸጸትን በትህትና ወደ እግዚአብሔር እንሩጥ፡፡ በቁጥር 51 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለ4ዐ ቀናት ያህል ለደቀመዛሙርቱ ከታየ በኋላ እንዲሁ ሁሉም በዐይናቸው እያዩት ወደ ሰማይ ወጣ፡፡ ነገር ግን በደቀመዛሙርቱ ሕይወት ውስጥ መሥርቱን እንደሚቀጥል ሐዋርያት ሥራ ይናገራል፡፡ ይሁንና አንድ ቀን ምጽዓት እንዳለም ተናግሯል፡፡ ዕርገቱ ለሐዋርያት ብቻ ሳይሆን ለአዳም ልጆች ሁሉ ትልቅ ጸጋ ሆኗል፡፡ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ በአዳም ኃጢያት ተዘግቶ የነበረውን የመንግስተ ሰማይ በር ከፍቶታል፡፡
ምንባቡ ስለምን ይናገራል?
በእየሩሳሌም ጀምሮ የተሰበከው ቃል ለኛ ምን ይህል ተሰብኳል?
እንዲሰበክስ ምንያደረግነው ነገር አልን?
የፊታችን ግንቦት አንድ ቀን የእናታችንን የድንግል ማርያምን የልደት በዓል እናከብራለን ና በረከተቷና አማላጅነቷ ከሁላችን ጋር ይሁን !